ሀዲያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ እውነታዎች እንደሚከተለው አጠናክረናቸዋል።

ሀዲያ ሆሳዕናዎች በባህር ዳር ከተረቱበት 11 ሦስት ተጫዋቾችን ለውጠው ለዛሬው ጨዋታ ቀርበዋል። በዚህም አይዛክ ኢሲንዴ፣ ብሩክ ቃልቦሬ እና ተስፋዬ አለባቸውን በፀጋሰው ፣ አማኑኤል ጎበና እና ዑመድ ኡኩሪ ለውጠዋል። የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለም የዛሬው ጨዋታ የወንድማማቾች ጨዋታ ነው የሚል ሀሳባቸውን በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ሰጥተው ለተጋጣሚ ቡድን አሠልጣኝ ገብረመድህን ያላቸውን አክብሮት በማስከተል የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልፀዋል።

በ1970ዎቹ አጋማሽ ከአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በጎጃም ምርጥ ቡድን ውስጥ እንደተጫወቱ ያስታወሱት አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በበኩላቸው አራፊ ከነበሩበት ጨዋታ በፊት ከተረጉበት ጨዋታ ስድስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም መሳይ አያኖ፣ ሰንደይ ሙቱኩ፣ ጊት ጋትኮች፣ ተመስገን በጅሮንድ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና ይገዙ ቦጋለን አሳርፈው ፍቅሩ ወዴሳ፣ አበባየሁ ዮሐንስ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ግርማ በቀለ፣ ኦኪኪ አፎላቢ እና ያሬድ ከበደ በመጀመርያ አሰላለፍ ተከተዋል።

ጨዋታውን ደረጄ ዋቅጋሪ በዋና ዳኝነት ይመሩታል

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሐመድ ሙንታሪ
30 አክሊሉ አያናው
15 ፀጋሰው ድማሙ
25 ተስፋዬ በቀለ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
14 መድሀኔ ብርሃኔ
10 አማኡኤል ጉበና
18 ዑመድ ኡኩሪ
13 አልሀሰን ካሉሻ
22 ቢስማርክ አፒያ
12 ዳዋ ሆቴሳ

ሲዳማ ቡና

1 ፍቅሩ ወዴሳ
21 አበባየሁ ዮሐንስ
2 ፈቱዲን ጀማል
7 ሽመልስ ተገኝ
19 ግርማ በቀለ
5 መሐሪ መና
16 ብርሀኑ አሻሞ
20 ዮናስ ገረመው
10 ዳዊት ተፈራ
8 ኢኪኪ አፎላቢ
34 ያሬድ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ