አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ጅማ አባጅፋር

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው ተሰናድተዋል።

በአዳማ ከተማ አንድ ለምንም ተረተው ውድድሩን የጀመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ጨዋታ ሦስት ለውጥ አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ክፍሌ ቦልተና የተሻ ግዛው፣ ፀጋ ደርቤ እና ነስረዲን ኃይሉን በማሳረፍ አቤል ታሪኩ፣ ብሩክ ጌታቸው እና አደም አባስ ወደ ቋሚ አሰላለፍ አምጥተዋል።

በመጀመሪያው ጨዋታ በዘንድሮ የውድድር ዘመን አብሯቸው በፕሪሚየር ሊጉ ሲወዳደር ከነበረው ወልቂጤ ከተማ ጋር የተጫወቱት ጅማ አባጅፋር ነጥብ ከተጋሩበት የዓርቡ ግጥሚያ ምንም የተጫዋች ለውጥ ሳያደርጉ ጨዋታውን ቀርበዋል።

በፌዴራል ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ በሚመራው ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ በቋሚ አሰላለፍ ለመጠቀም ወደ ሜዳ ያስገቧቸው ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ

30 ዘሪሁን ታደለ
16 ሀብታሙ ጥላሁን
28 ብሩክ ጌታቸው
21 ወልደአማኑኤል ጌቱ
13 ፍራኦል መንግሥቱ
24 ቢኒያም ትዕዛዙ
6 እንዳለ ዘውገ
19 ሳሙኤል ታዬ
3 አቤል ታሪኩ
9 ኤርሚያስ ኃይሉ
7 አደም አባስ

ጅማ አባጅፋር

91 አቡበከር ኑሪ
28 ሥዩም ተስፋዬ
16 መላኩ ወልዴ
14 ኤልያስ አታሮ
3 አሌክስ አሙዙ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
13 ዋለልኝ ገብሬ
20 ሀብታሙ ንጉሤ
19 ተመስገን ደረሰ
3 ራሂም ኦስማኖ
26 ዋውንጎ ፕሪንስ