የንግድ ባንክ አሰላለፍ ታውቋል

10:00 ላይ ወሳኝ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይዞት የሚገባው አሰላለፍ ታውቋል።

በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣርያ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ንግድ ባንክ የዩጋንዳው ሌዲ ዶቭስን የሚገጥም ሲሆን ለዚህ ጨዋታሜ አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው ለውጦች በማድረግ ትዕግስት ኃይሌ፣ ንግስት መዓዛ፣ ሕይወት ደንጊሶ፣ ዓለምነሽ ገረመው እና ፀጋነሽ ወራና አራፊ የሆኑ ሲሆን በምትኩ ታሪኳ በርገና፣ ትዝታ ኃይለሚካኤል፣ ብዙዓየሁ ታደሰ፣ ሰናይት ቦጋለ እና አረጋሽ ካልሳ ወደ አሰላለፉ መጥተዋል።

ግብ ጠባቂ

ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ታሪኳ ዴቢሶ
ሀሳቤ ሙሶ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
ብዙዓየሁ ታደሰ

አማካዮች

ትዕግስት ያደታ
እመቤት አዲሱ
ሰናይት ቦጋለ

አጥቂዎች

አረጋሽ ካልሳ
መዲና ዐወል
ሎዛ አበራ