አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ሰበታ ከተማ ከ መከላከያ

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ ተከታዮቹን መረጃዎች አዘጋጅተንላችኋል።

በመጀመሪያው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ የተጋራው ሰበታ ከተማ ቀይ ካርድ የተመለከተው አንተነህ ተስፋዬ እና ዘካሪያስ ፍቅሬን በፍፁም ገብረማሪያም እና ጁኒያስ ናንጄቤ በመተካት ጨዋታውን በማጥቃት ላይ የተመሰረቱ ለውጦች በማድረግ ለመጀመር ተዘጋጅቷል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት ለውጥ ያደረጉት መከላከያዎች አርባምንጭን ካሸነፉበት ጨዋታ በደሳለኝ ደባሽ እና በድንገተኛ ምክንያት ከጨዋታ ውጪ በሆነው ቢኒያም በላይ ምትክ በመጀመሪያው ጨዋታ ተቀይረው ገብተው የነበሩት አዲሱ አቱላ እና ብሩክ ሰሙን ወደ አሰላለፍ አምጥተዋል።

ፌደራል ዳኛ ሄኖክ አክሊሉ ይህንን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበውል።

ሰበታ ከተማ

30 ለዓለም ብርሀኑ
5 ጌቱ ኃይለማሪያም
15 በረከት ሳሙኤል
12 ቢያድግልኝ ኤሊያስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
27 ክሪዚስቶም ንታንቢ
18 አብዱልሀቪዝ ቶፊቅ
7 ዱሬሳ ሹቢሳ
9 ሳሙኤል ሳሊሶ
16 ፍፁም ገብረማሪያም
20 ጁኒያስ ናንጄቤ

መከላከያ

30 ክሌመንት ቦዬ
11 ዳዊት ማሞ
4 አሌክስ ተሰማ
2 ኢብራሂም ሁሴን
13 ገናናው ረጋሳ
25 ኢማኑኤል ላሪያ
10 አዲሱ አቱላ
7 ብሩክ ሰሙ
14 ሰመረ ሀፍተይ
5 ግሩም ሀጎስ
18 ኦኩቱ ኢማኑኤል