የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

የሳምንቱ ተጠባቂው ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸነፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞቹ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ጨዋታው እንደተጠበቀው ከባድ ነበር ?

“እንዳልኩት ነው ከእኛ ጋር ሲጫወቱ ሁሉም ቡድኖች ጠንካራ ናቸው። ሲዳማ ቡና ጠንካራ ቡድን እንደሆነ እናውቃለን። ከባድ ጨዋታ ነው። በከባድ ጨዋታ ደግሞ ሁሉን ነገር ተቋቁሞ ማሸነፍ ትልቅ ነገር ነው። ይሄንን ድል ተቀናጅተናል።

የዛሬው ሦስት ነጥብ አስፈላጊነቱ ?

“ይህ ነጥብ ከሚከተሉን ተጋጣሚዎቻችን ከሲዳማ ቡና ማሸነፍ በድል መወጣት ትልቅ አስተዋፆኦ ያለው በመሆኑ ልጆቼም ተጋድሎ አድርገው አሸንፈን ስለወጣን በጣም ደስ ብሎኛል።

በቁጥር ማነሳቸው ስለፈጠረው ጭንቀት ?

” ይጨንቃል አንድም ሰው በመሆንህ እንደ ተጫዋች የምታስብበት መንገድ አለ። ግን ተጫዋቾቹን አረጋግተናቸው የሰጠናቸው ክፍት ቦታ የለም። የመከላከል አደረጃጀታችን ዘግተን ነበር የተጫወትነው አንድነታችን እና የመጫወት ፍላጎታችን ምሳሌ ስለሚሆን ይህ አልፏል ለሚቀጥለው ጨዋታ እራሳችንን አዘጋጅተን የተሻለ ነገር አድርገን እንመጣለን።”

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና

ጨዋታው በታሰበው ልክ ተተግብሯል ?

” አልተተገበረም። መጀመርያ ጨዋታውን ተቆጣጥረን ለመጫወት ነው አቅደን የመጣነው። ይህን ደግሞ ብዙ መልኩ አልተገበርንም። ምን ማለት እንደምችል አላቅም። በጣም የተቆራረጡ ኳሶች ለሚፈለው ሰው የማድረስ ችግር ነበረ። ሙሉ ብልጫ ወስደን ወደ ባላጋራ የሜዳ ክፍል ለመግባት ነበር ጥረት አስበን የገባነው። ይሄ ደግሞ ተግባራዊ አልሆነም። ከዕረፍ በኋላ መጥፎ ሰዓት ላይ ጎሉ ስለገባ ጥሩ አልነበረም። እርስ በእርስ ባለመግባባት ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ለማስተካከል ጥረት አድርገናል። ሙሉ ብልጫውን ብንወስድም ማግባት አልቻልንም። ጥቅጥ ብለው የመከላከል ባህሪ ስላላቸው ያው ቅዱስ ጊዮርጊስ በመከላከሉ ጥሩ ስለሆኑ ያንን ማሸነፍ አልቻልንም። በአጠቃላይ ብንሸነፍም መጥፎ የሚባል አይደለም።

የተጫዋች ቅያሪ ማጥቃትን በማሰብ ነው ?

” አዎ ግልፅ ነው። እርሱ ብቻ ሳይሆን የመስመር ተከላካይ በመቀነስ ከኋላ እየተነሳን ለማጥቃት ባህሪ ያላቸውን ተጫዋቾች ገብተው ነበር። እርሱን ተግባራዊ ስናደርግ ጥሩ ነበርን። ነገር ግን አንዳንድ ኳሶች በትክክል ያለ መሄድ ችግር ነበር። ከመስመር የሚወጡ ኳሶች ጥሩ አልነበሩም እንጂ ጥሩ ነው።

በዋንጫው ፉክክር ስለ መቆየት ?

” ከዚህ ቀደም ተናግሬአለው። ምንም የማይፈጠር ነገር የለም። የአስራ አንድ ነጥብ ልዮነት አለን ሊሆን ይችላል። ግን እኛ መጀመርያም ዛሬም ቢሆን ቅዱስ ጊዮርጊስን ብናሸንፍም እነርሱን ለመቅደም ብቻ አይደለም ግባችን። የአሸናፊነት ስሜታችንን ማስቀጠል፣ ሁለተኛ አጠገባችን ያሉትን ቡድኖች ከእነርሱ ወጣ ብለን ለመገኘት መቻል፣ ከዛ በኋላ ነው ስለሌላው ማሰብ የምትጀምረው። ከዚህ ውጭ ሩቅ ነው ከዚህ በኋላ የሚቀረን አስር ጨዋታ ነው። አስቸጋሪ ቢሆንምየምንፈልገውን ሁለተኛ ሦስተኛ ደረጃ የመውጣት ህልማችንን ማሳካት እንችላለን ብዬ አስባለው።”