ቡናማዎቹ የኤርትራዊውን አማካይ ውል አደሱ

በኢትዮጵያ ቡና ሁለት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈው ሮቤል ተክለሚካኤል ውሉን ለተጨማሪ ዓመት አራዘመ፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣዩን ዓመት በጠንካራ ተፎካካሪነት ለመዝለቅ ብርቱ ዝውውሮችን እየፈፀመ የሚገኘው ኢትዮጽያ ቡና የአማካዩ ሮቤል ተክለሚካኤልን ውል ማደሱን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ከኤርትራው ቀይ ባህር ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በኢትዮጵያ ቡና ጥሩ ሁለት ዓመታትን አሳልፎ የነበረው ይህው ተጫዋች ለተጨማሪ ሁለት ዐመት በክለቡ እንደሚቀጥል ተረጋግጧል፡፡