መቻል ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

ረፋድ ላይ ተክለማርያም ሻንቆን የግሉ ያደረገው መቻል ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመራው መቻል የቀጣይ ዓመት ስብስቡን እያጠናከረ የሚገኝ ሲሆን እስካሁንም አህመድ ረሺድ ፣ ቶማስ ስምረቱ ፣ ተስፋዬ አለባቸው ፣ ከነዓን ማርክነህ ፣ ፍፁም ዓለሙ ፣ ምንይሉ ወንድሙ ፣ ዳግም ተፈራ ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ ፣ በረከት ደስታ ፣ ውብሸት ጭላሎ እና ግርማ ዲሳሳን ማስፈረሙ ይታወቃል። በተጨማሪም ረፋድ ላይ ተክለማርያም ሻንቆን የግሉ ያደረገው ቡድኑ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ጥሩ ብቃት ያሳየውን አማካይ 13ኛ ፈራሚው አድርጓል።

ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች በሀይሉ ኃይለማርያም ነው። ከመከላከያ ተስፋ ቡድን የተገኘው በሀይሉ 2010 ላይ ወደ የካ ክፍለ ከተማ አምርቶ የነበረ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ግልጋሎት ሰጥቶ ነበር። አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል የመቻል አባል ሆኗል።