ከሱዳን ጋር ለሚደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

ከቀናት በኋላ ከሱዳን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ የሚያደርገውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለይተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ወቅትን በመጠቀም ከሱዳን ብሄራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ከጫፍ እንደደረሰ ሶከር ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት ዘገባ ሰርታ ነበር። ከሱዳን ብሔራዊ ፌዴሬሽን ባገኘነው መረጃም ብሔራዊ ቡድኑ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረቡን አመላክተን ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ዓርብ መስከረም 13 እና ሰኞ መስከረም 16 አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ለሚደረጉት ጨዋታዎች አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች


ግብ ጠባቂዎች

በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሰኢድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ)፣ ዳንኤል ተሾመ (ድሬደዋ ከተማ)

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሱሌማን ሃሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና) ፣ አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ) ፣ ፍሬዘር ካሳ (ሀዲያ ሆሳእና)

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ሽመልስ በቀለ (ኤል ጉውና/ግብፅ) ፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፣ በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ) ፣ ታፈሰ ሰለሞን (ፋሲል ከነማ) ፣ መሱድ መሀመድ (አዳማ ከነማ) ፣ ከነአን ማርክነህ (መቻል)

አጥቂዎች

በረከት ደስታ (መቻል) ፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ) ፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና) ፣ ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች በነገው ዕለት ሪፖርት በማድረግ በጁፒተር ሆቴል ተሰባስበው ልምምድ እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።