ቻን | ወሳኙን የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ጨዋታ ጋቦናዊ አልቢትር ይመሩታል

ነገ ምሽት 4 ሰዓት በኢትዮጵያ እና አልጄሪያ መካከል የሚደረገውን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

\"\"

በሀገር ውስጥ ሊጎች ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት 7ኛው የቻን ውድድር በአልጄሪያ አዘጋጅነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ሀገራችን ኢትዮጵያም የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሞዛምቢክ ጋር አድርጋ ያለ ግብ የተለያየች ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ ሁለተኛ መርሐ-ግብሯን ከአስተናጋጇ ሀገር አልጄሪያ ጋር ምሽት 4 ሰዓት በውቡ ኔልሰን ማንዴላ ስያሜ በተሰጠው ስታዲየም ታደርጋለች። ይህንን ወሳኝ ጨዋታ ደግሞ ጋቦናዊው አልቢትር ፒየር ጂስሌን አትቾ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ታውቋል።

\"\"

ፒየር አትቾን የሀገራቸው ልጅ ዲስቶጋ ቦሪስ እና የሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዜግነት ያላቸው ሬይስ ሚሮ በረዳትነት እገዛ ሲሰጡዋቸው የጨዋታው አራተኛ ዳኛ ደግሞ ከሞሪሺየስ እንደተመደቡ ተገልጿል። በቪ ኤ አር ዳኝነት ቦታ ላይ ደግሞ ቱኒዚያዊው ሀይተም ጉኢራት ይሰየማሉ።