ሲዳማ ቡና ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

በርካታ ክለቦች በማሰልጠን የሚታወቁት አሰልጣኝ የሲዳማ ቡና ረዳት አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

\"\"

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድር ጠንካራ ተሳትፎን ለማድረግ የወጠነው ሲዳማ ቡና ከቀናት በፊት በአንደኛው ዙር ያላደረገውን ተስተካካይ ጨዋታ ከወላይታ ድቻ ጋር አድርጎ ነጥብ የተጋራ ሲሆን የሁለተኛውን ዙር የሊግ ጨዋታ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ለገጣፎ ለገዳዲን በማስተናገድ ይጀምራል። በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ስር በረዳት አሰልጣኝነት ቾንቤ ገብረህይወት እንዲሁም በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ደግሞ ስንታየው ግድየለው የሚገኙ ሲሆን አሁን በዋናው አሰልጣኝ ምርጫ ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝን ክለቡ ሾሟል።

በረዳት አሰልጣኝነት ሚና የተሾሙት አረጋዊ ወንድሙ ናቸው። እርሻ ሰብል ፣ ጅማ አባቡና ፣ ጥቁር አባይ ፣ አማራ ፓሊስ ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፣ አድዋ ፣ ወልድያ ከተማ ደሴ ከተማ እና ቤንች ማጂ ቡናን በአሰልጣኝነት መርተው ያሳለፉት አሰልጣኙ ሲዳማ ቡናን በይፋ ተቀላቅለዋል።

\"\"

ክለቡ ከረዳት አሰልጣኙ ሹመት በተጨማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ኢሳያስ ኃይሌ የተባለ የኒውትሪሽን ባለሙያን ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ቀጥሯል።