የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የመርሐ ግብር ማስተካከያ ተደርጓል

በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የቦታ ለውጥ ተድርጓል።

\"\"

ከትናንት በስትያ በተደረጉ ጨዋታዎች 21ኛ ሰምንቱን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ነገ በ22ኛ ሳምንት እንደሚቀጥል እየተጠበቀ ይገኝ ነበር። ሆኖም ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ነገ እና ከነገ በስትያ ሊደረጉ የታሰቡት ጨዋታዎች የቀን እና የቦታ ለውጥ ተደርጎባቸል።

የውድድሩ አዘጋጅ እና ሥነስርዓት ኮሚቴ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ለተወዳዳሪ ክለቦች በላከው ደብዳቤ መሰረት ነገ ሚያዚያ 04 ይከናወኑ የነበሩ ጨዋታዎች የሰዓት ለውጥ ሳይደረግባቸው ሚያዚያ 06 በአፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል። በተመሳሳይ ለሚያዚያ 05 ቀነ ቀጠሮ የተያዘላቸው ጨዋታዎች ደግሞ የሰዓት ለውጥ ሳይደረግባቸው ሚያዚያ 06 በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እንደሚደረጉ ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ ኮሚቴው ለውጦቹን ለማድረግ ስላስፈለገበት ምክንያት ያለው ነገር የለም።

\"\"

በመጀመሪያ ዙር በሀዋሳ በሁለተኛ ዙር ደግሞ በባህር ዳር ቆይታ ያደረገው ውድድሩ የሦስት ሳምንት ጨዋታዎችን ካስተናገደ በኋላ በያዝነው ወር መጨረሻ እንደሚገባደድ ይጠበቃል።