የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልቂጤ ከተማ 0-0 ፋሲል ከነማ

\”ወራጁን እንኳን አሁን ሳይሆን በመጨረሻው ቀን ነው የሚለየው ብዬ አስባለሁ\” አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ

\”ከታች የመጣ ነው ፣ ስሜቱን እረዳዋለሁ ፣ ግን ምንም እስካልሰራ ድረስ ከቡድኑ ማንም አይበልጥም\” አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ

ወልቂጤ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የሀዋሳ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያለ ጎል ከፈፀሙ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – ወልቂጤ ከተማ

ስለ ተወሰደባቸው ብልጫ እና በመጨረሻው ደቂቃ ስለነበራቸው መሻሻል…

\”ጨዋታው ጥሩ ነው ምክንያቱም እነርሱ ሁለት ጨዋታ ተሸንፈው መጥተዋል። ስለዚህ ጠንክረው እንደሚጫወቱ እናውቃለን ፣ ግን ደግሞ እኛም አቡበከር ያገኛቸውን ኳሶች አግብተን ቢሆን ኖሮ የጨዋታውን አቅጣጫ ይቀየር ነበር። ጥሩ ነው የምለው እኛ አሁን እያደረግን ያለነው ነገር ተጫዋቾቼ እያደረጉት ያለውም ነገር ለቡድኔ አስተማማኝ ነው ብዬ የማስበው እና ጥሩ እንቅስቃሴ ነው ከዕረፍት በፊት ግን አንዳንድ ታክቲካል የሆኑ ችግሮች ነበሩብን በእዛ ምክንያትም ነው ተጫዋቾቼ የተዘናጉት ከዕረፍት በኋላ አስተካክለነዋል ብዬ አስባለሁ።\”

\"\"

ስለ ቡድኑ መሻሻል እና በሊጉ የመቆየት ተስፋ…

\”በሚገባ ምንም አያጠራጥርም እኮ ምልክቱ የሚያደርጉት ነገር ነው። ስለዚህ ለመውረድ
ያለው ቡድን እኛ ወይንም አንድ አይደለም ስድስት እና ሰባት ቡድን በዚህ ዞን ውስጥ ነው ያለው ፣ አንድ ጨዋታ ካሸነፍክ ታመልጣለህ አንድ ስትሸነፍ ትወርዳለህ ፣ ሊጉ አንድ ዓይነት የተጨናነቀ ስለሆነ ብዙም ወራጁን እንኳን አሁን ሳይሆን በመጨረሻው ቀን ነው የሚለየው ብዬ አስባለሁ።\”

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ፋሲል ከነማ

ቡድኑ ስለ ነበረው ብልጫ እና መጨረሻ ላይ ስለታየው መቀዛቀዝ…

\”በጨዋታው እንደ ቡድን ቡድናችን ጥሩ ነው። ትልቅ ችግር ያለው አጨራረስ ላይ ነው። ይሄ ጨዋታ በስንት ጎል ማለቅ እንዳለበት መገመት አያቅትህም ዞሮ ዞሮ ግን ጥሩ ጨዋታ ነው።\”

የሀዋሳ ቆይታቸው የተሳካ ስላለመሆኑ..?

\”የተሳካ ጊዜ ነው ለማለት አያደስፍርም ያሉንን ነገር ተቀብለን ውድድሩን መጨረሻችን መልካም ነው።\”

\"\"

ናትናኤል ማስረሻ ተቀይሮ ገብቶ ተቀይሮ ሲወጣ በእምባ ስለወጣበት መንገድ…

\”እግርኳስ እኮ ሚስጥር አይደለም። የምታየው ነገር ነው ፣ የጠበኩት እና የሰራው ነገር ምን አለ ? በጎዶሎ ልጅ ከመጫወት የገባው ልጅ የተሻለ ትግል አድርጓል። ስለዚህ ከዚህ አኳያ ነው እንጂ በሌላ መልኩ አይደለም። አስገብተን እንደዚህ ሲቀየር ስናስወጣው ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። አንድ ተጫዋች ምንም ካልሰራልህ ምንድነው የምታደርገው በዚህ ላይ ከታች የመጣ ነው ስሜቱን እረዳዋለሁ ፣ ግን ምንም እስካልሰራ ድረስ ከቡድኑ ማንም አይበልጥም።\”