ሪፖርት | የወልቂጤ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ ያለ ጎል ተጠናቋል

የወልቂጤ እና ፋሲል የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት ፍፃሜን አግኝቷል።

ወልቂጤ ከተማ ድል ካደረጉበት የመድኑ ጨዋታቸው ቅያሪ ሳያደርጉ ሲገቡ በአንፃሩ ከድሬዳዋው ሽንፈታቸው ፋሲሎች የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጡም አስቻለው ታመነን በዓለምብርሀን ይግዛው ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝን በዱላ ሙላቱ ተክተዋል።

\"\"

ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የዕለቱ ዋና ዳኛ ተካልኝ ለማ ፋሲሎች ያደረጉት መለያ ከወልቂጤ ጋር ተመሳሳይ መልክ አለው ለመለየት ምቹ አይደለም በሚል ከተያዘለት ሰዓት አስራ ስምንት ያህል ደቂቃዎች ከዘገየ በኋላ ጨዋታው ተጀምሯል። የፋሲል ከነማ የእንቅስቃሴ የበላይነት በጉልህ በተንፀባረቀበት የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ከሚደረጉ የሜዳ ላይ የኳስ ቅብብሎች ውጪ አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ሳይደረግበት የተገባደደ ነበር። መሐል ሜዳ ላይ መነሻቸውን ካደረጉ የጥቃት ምንጮች ወደ መስመር በማድላት ለመጫወት የዳዱት ፋሲሎች ከሚታወቅበት ቦታው ወደ መሐል ገብቶ ሲጫወት የነበረው ሽመክት እና ሱራፌል በኋላም በሁለቱ መስመሮች ናትናኤል እና ዓለምብርሀንን በይበልጥ ሊጠቀሙ ያሰቡት ፋሲሎች በተሻለ ወደ ጎል ደርሰዋል።

\"\"

በአንፃሩ የፋሲልን የሚቋረጡ ኳሷን በቶሎ ሲያገኙ በሽግግር ሲጫወቱ የነበሩት ወልቂጤዎች 39ኛው ደቂቃ ተመስገን አሻምቶ አስራት ገጭቶ ኢላማ ካልጠበቀችባቸው ሙከራ ውጪ እምብዛሞች ነበሩ። በንፅፅር በተሻለ በዓለምብርሀን ሲያጠቁ ጥሩ የነበሩት ፋሲሎች ተጫዋቹን በጉዳት ካጡት በኋላ በዱላ አማካኝነት በተደጋጋሚ ቀዳዳ ሲፈልጉ ቢታይም የነበረባቸው ደካማ የውሳኔ አሰጣጥ እንደ ነበራቸው ብልጫ እንዳያስቆጥሩ አድርጓቸዋል። ሽመክት ጉግሳ ከርቀት ሞክሮ የግቡን ቋሚ ታካ ከወጣችዋ ሙከራ ውጪ ጥራት ባለው ሙከራ ያልታጀበው አጋማሽ 0ለ0 ለዕረፍት አምርቷል።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ሲቀጥል በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ከነበረባቸው ድክመት ወልቂጤዎች ተሻሽለው መቅረብ የቻሉበት ሲሆን ጉዳት የገጠመው ተመስገንን በፋሲል በመተካትም ነበር ጨዋታቸውን የቀጠሉት መሐል ሜዳ የአማካዩን ብዙአየው ሰይፈን ግልጋሎት በይበልጥ በመጠቀም በመጨረሻም ጌታነህ እና አቤል መዳረሻለው አድርገው የማንቀሳቀሱት ወልቂጤ ከተማዎች በቀላሉ በቅብብል የፋሲል ሜዳ ላይ ሲደርሱ ይታይ እንጂ የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ደካሞች ናቸው። በተወሰነ መልኩ አጀማመራቸውን በተቀዛቀዘ መልኩ ያደረጉት ፋሲሎች በተሻጋሪ እና በመልሶ ማጥቃት ተጫውቶ ግብን ለማስቆጠር የሄዱበት ውጤታማ ሊያደርጋቸው ተቃርቦ ነበር።

\"\"

58ኛው ደቂቃ ላይ በዚህ የጨዋታ መንገድ የወልቂጤው ተከላካይ አዲስዐለም ተስፋዬ ከራሱ ሜዳ ኳስን ለማራቅ ሲሞክር በማውሊ በመነጠቁ ጋናዊው አጥቂ ወደ ሳጥኑ እየገፋ ደርሶ ወደ ግብ ሲሞክር ኳሷ አቅጣጫ ቀይራ ወጥታለች። ወልቂጤዎች የፋሲሉ ተከላካይ ዳንኤል ፍፁም ባልተረጋጋበት ወቅት አቡበከር ሳኒ በቀላሉ ወደ ጎልነት መለወጥ የሚችልበትን ዕድል ሊጠቀምበት አልቻለም በቸሻለ የማጥቃት ወጥነት ከቆመ እና ከሚሻገሩ ኳሶች ጥቃት የሚሰነዝሩት ፋሲሎች 58ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ናትናኤል ማስረሻን 78ኛው ደቂቃ ላይ በድጋሚ ተቀይሮ ሲወጣ በእምባ ከሜዳ የወጣበት አጋጣሚ የጨዋታው ሌላኛዋ ክስተት ነበረች። ፋሲሎች ሱራፌል ከቅጣት አሻምቶ ማውሊ ገጭቶ የወጣበት እና ማውሊ በሌላ በኩል አሻምቶ ዱላ ፋሪስን ያሳቀፈበት መንገድ ሌላኛዋ ዕድላቸው ነበረች።

ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተሰጠው የጭማሪ ደቂቃ ወልቂጤዎች በጌታነህ ከበደ ከቅጣት እና ከማዕዘን ምቶች ሦስት አጋጣሚዎችን አከታትለው የፈጠሩ ቢሆንም ሚካኤል ሳማኪ ካወጣቸው በኋላ ጨዋታው 0ለ0 ሊጠናቀቅ ችሏል።

\"\"