የትግራይ ጊዜያዊ መስተዳድር ለኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ደብዳቤ ላከ

የማሕበራዊ ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተርያት የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍ ጠይቋል።
\"\"
የትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከወራት በፊት በሚያዝያ 19 ጦርነቱ በክልሉ ያደረሰውን ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ውድመት በመጥቀስ የክልሉን ስፖርት እንቅስቃሴ ዳግመኛ እንዲጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በደብዳቤ መግለፃቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በጊዜያዊ መስተዳድሩ ስር ያለው የማሕበራዊ ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተርያት ከፌደሬሽኑ ምላሽ እንዳላገኙ በመጥቀስ በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት የደረሰባቸው የክልሉ ክለቦች በቀጣይ ዓመት ወደ ሊግ ውድድሮች እንዲመለሱ ሚኒስተር መስርያ ቤቱ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል።
\"\"
እንቅስቃሴ ለመጀመር በጥረት ላይ ያሉ የትግራይ ክለቦች በቀጣይ ዓመት ወደ ውድድር ለመመለስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ወልዋሎ ዓድግራት ዩንቨርስቲ የውስጥ ውድድር በማድረግ ላይ ሲገኝ ስሑል ሽረዎችም ቀደም ብለው ልምምድ መጀመራቸው ይታወቃል።