ባህርዳር ከተማ የመስመር ተከላካዩን ውል አድሷል

ወደ ዝውውሩ በዛሬው ዕለት የገባው ባህርዳር ከተማ የመስመር ተከላካዩን ውል አድሷል።
\"\"
በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህርዳር ከተማ የመስመር ተከላካዩን ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ውሉን አድሶለታል። ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ያገለገለው እና በሀምበሪቾ ዱራሜም የመጫወት ዕድል የነበረው መሳይ አገኘሁ በጣና ሞገደኞቹ ቤት ውሉ መጠያቀቁን ተከትሎ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ውሉ ተራዝሟለታል።
\"\"
ክለቡ በዛሬው ዕለት የፍሬው ሰለሞንን ዝውውር ሲፈፅም ከቸርነት ጉግሳ ጋር መስማማቱን ገልፀን እንደነበር ይታወሳል።