ወልቂጤ ከተማዎች ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል

ሠራተኞቹ ዘጠኝ ተጫዋቾች ስያስፈርሙ የሁለት ጫዋቾች ውል አድሰዋል።

ቀደም ብለው ሙልጌታ ምህረትን ዋና አሰልጣኝ አድርገው የሾሙት ወልቂጤዎች ዘጠኝ ተጫዋቾች አስፈርመው የሁለት ነባር ተጫዋቾች ውል አድሰዋል። የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ባህርዳር ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና አማካይ ሳምሶን ጥላሁን፤ የቀድሞ የወላይታ ድቻ አጥቂ ስንታየሁ መንግስቱ፤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ የመሀል ተከላካይ መሳይ ጻውሎስ፤ የቀድሞ የቅዱስ ግዮርጊስ እና አዳማ ከተማ አጥቂ አሜ መሐመድ፤ በኢትዮጵያ ቡና፣ ወልዲያ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና አዳማ ከተማ ቆይታ የነበረው አማካዩ ዳምኤል ደምሱ፤ የቀድሞ የሰበታ እና ኤሌክትሪክ የመስመር ተከላካይ ጌቱ ኃይለማርያም፤ አማካዩ በቃሉ ገነነ፤ የመስመር አጥቂዎቹ ራምኬል ሎክ እና ጋዲሳ መብራቴ በዛሬው ዕለት ለክለቡ ፊርማቸው ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ክለቡ ከዘጠኙ ተጫዋቾች በተጨማሪ የግብ ጠባቂው ፋሪስ አላዊ እና አጥቂው አቡበከር ሳኒን ውል አድሷል።