ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

በትላንትናው ዕለት ወደ ዝውውሩ የገቡት ወልቂጤ ከተማዎች አስረኛ ፈራሚያቸው አግኝተዋል።

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን የክለቡ አለቃ አድርገው ከቀናት በፊት የቀጠሩት ወልቂጤ ከተማዎች ዘግይተውም ቢሆን ወደ ዝውውሩ በመግባት በትላንትናው ዕለት የዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቁ ሲሆን አሁን ደግሞ አስረኛ ፈራሚ በማድረግ ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖን ተቀላቅለዋል።

የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ፣ አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ የነበረው መሳይ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሀድያ ሆሳዕና ቤት ቆይታን ካደረገ በኋላ በሀድያ ካሰለጠኑት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ጋር ዳግም የተገናኘበትን ዝውውር ቋጭቷል።