የጣና ሞገዶቹ ጨዋታ በዝግ ስታዲየም ይደረጋል

በነገው ዕለት ከታንዛኒያው አዛም ክለብ ጋር የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታቸውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚያደርጉት ባህር ዳር ከተማዎች በዝግ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ባህር ዳር ከተማዎች ሀገራችንን በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ እንደሚወክሉ ይታወቃል። በውድድሩ የቅድመ የማጣሪያም ነገ ከታንዛኒያው አዛም ክለብ ጋር የሚጫወቱ ሲሆን ተጋጣሚያቸውም ትናንት ረፋድ አዲስ አበባ ገብቷል።

ቀደም ብሎ ይህ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም እንደሚደግ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ወደ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደዞረ ይታወቃል። ድረ-ገፃችን ሶከር ኢትዮጵያ አሁን በደረሳት መረጃ መሠረት ነገ 10 ሰዓት የሚደረገው ጨዋታው ያለ ደጋፊ በዝግ ስታዲየም ይከወናል።