አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

አዳማ ከተማዎች ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ ከታዳጊ ቡድን ደግሞ አራት ተጫዋቾችን አሳድገዋል።

በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አዳማ ከተማ በዝውውር መስኮቱ እስካሁን ሱራፌል ዐወል ፣ አሸናፊ ኤልያስ ፣ ፍቅሩ አለማየሁ ፣ መላኩ ኤልያስ ፣ ተክለማርያም ሻንቆ ፣ ኤፍሬም ዘካሪያስ፣ አቡበከር ሻሚል እና አህመድ ረሺድን ወደ ስብስቡ መቀላቀሉን ገልፀን ነበር። አሁን ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሠረት ደግሞ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች እንዲሁም አራት የታዳጊ ቡድን ተጫዋቾች ዋናውን ስብስብ ተቀላቅለዋል።

በ2015 በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ያሳለፉት የቀኝ መስመር ተከላካዩ ተስፋሁን ሲሳይ እንዲሁም የመሐል ተከላካዩ ሬድዋን ሸሪፍ ክለቡን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅለዋል።

በተጠናቀቀው ዓመት በርካታ ወጣት ተጫዋቾችን በቡድናቸው ያሳዩን አሠልጣኝ ይታገሱ አሁንም ከታዳጊ ቡድናቸው አራት ተጫዋቾችን አሳድገዋል። በዚህም መሐሪ ክፍሌ፣ ሙባረክ ሸምሱ፣ ጆቴ አዱኛ እና ተከተል አዱኛ ዋናውን ቡድን ተቀላቅለው ልምምዳቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።