ወደ ታንዛኒያ የሚያቀናው የባህር ዳር ከተማ ቡድን አባላት ታወቁ

የኮንፌዴሬሽን ካፕ የመልስ ጨዋታ የሚጠብቃቸው ባህር ዳር ከተማዎች 49 የልዑካን ቡድን በመያዝ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ።

በአሠልጣኝ ደግረአረ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር እንደሚሳተፍ ይታወቃል። በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያም ከታንዛኒያው አዛም ጋር የተደለደለው ክለቡ ባሳለፍነው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታውን አከናውኖ 2ለ1 ያሸነፈ ሲሆን የፊታችን ዓርብ ደግሞ ታንዛኒያ ላይ የመልሱን ጨዋታ ያከናውናል።

ከእሁዱ ጨዋታ ማግስት ከሱዳኑ ክለብ ሀይዱብ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርጎ (በዕሁዱ ጨዋታ ያልተሰለፉ ተጫዋቾች የተሳተፉበት) 1ለ0 ያሸነፈው ባህር ዳር በትናንትናው ዕለት ለተጫዋቾች ዕረፍት በመስጠት ልምምድ አልከወነም።

የፊታችን ዓርብ በዳሬ ሰላም ቻማዚ ኮምፕሌክስ ስታዲየም ወሳኝ ጨዋታውን የሚያደርገው ስብስቡም በሁለት ዙር ተከፍሎ ታንዛኒያ ይደርሳል። ትናንት ለሊት 6 ሰዓት የሥነ-ምግብ ባለሙያን ጨምሮ አጠቃላይ 10 የሚጠጉ የአስተዳደር ሰዎች ቀድመው ወደ ስፍራው ያቀኑ ሲሆን ቡድኑ የሚያርፍበትን ሆቴል እና ሌሎች ጉዳዮችን እያመቻቹ እንደሚቆዩ ታውቋል። ዛሬ ደግሞ ከሰዓታት በኋላ ረፋድ 4 ሰዓት ላይ ተጫዋቾች፣ የአሠልጣኝ ቡድን አባላት፣ የቦርድ አባላት እና የደጋፊ ማኅበር አመራሮች ወደ ስፍራው ያቀናሉ። በአጠቃላይ 49 የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ስፍራው እንደሚያመሩም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ተጫዋቾች እና የአሠልጣኝ ቡድን አባላት ከስር ተጠቅሰዋል።

ግብ ጠባቂ

አላዛር ማርቆስ
ፓፔ ሰይዱ
ይገርማል መኳንንት

ተከላካዮች

ያሬድ ባየ
መሳይ አገኘሁ
ፍሬዘር ካሣ
ሳለአምላክ ተገኘ
ፍራኦል መንግስቱ
ዳዊት ወርቁ

አማካዮች

አለልኝ አዘነ
የአብስራ ተስፋዬ
በረከት ጥጋቡ
ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
ፍሬው ሠለሞን

አጥቂዎች

ቸርነት ጉግሳ
ፍፁም ጥላሁን
ሀብታሙ ታደሠ
አደም አባስ
ዱሬሳ ሹቢሳ
ሱሌይማን ትራኦሬ

የአሠልጣኝ ቡድን አባላት

ደግአረገ ይግዛው – ዋና አሠልጣኝ
ደረጄ መንግስቱ – ምክትል አሠልጣኝ
አባይ ባዘዘው – ፊዚዮቴራፒስት
አሻግሬ አድማሱ – የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ
መብራቱ ሀብቱ – የአካል ብቃት አሠልጣኝ
ታደሠ ምትኩ – ዶክተር
ሔኖክ ሀብቴ – የቡድን መሪ
ተስፋዬ ብርሀኔ – የሥነ-ምግብ ባለሙያ