መቻሎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

ቀደም ብለው በርከት ያሉ ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቀቁት መቻሎች አንድ ተጫዋቾች ሲያስፈርሙ የነባር ተጫዋች ውልም አራዝመዋል።

በአሰልጣኝ ስለሺ ገመቹ የሚመሩት መቻሎች ስብስባቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል። አሁንም አንድ ተጫዋች ሲያስፈርሙ የነባር ተጫዋች ውል አድሰው አንድ ተጫዋች ደግሞ ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል።

ቀደም ብሎ አዳዲስ ተጫዋቾች ጨምሮ የነባሮቹን ውል ያደሰው ክለቡ የቀኝ መስመር ተከላካይዋ ዙርያሽወርቅ መልኬን ውል ስያድስ በአዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ቆይታ የነበራት አጥቂዋ አብነት ጎበናን አስፈርሟል። በአጥቂ ስፍራ ላይ የምትጫወተው ማርያማዊት ስመኝ ደግሞ ከታዳጊ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን አድጋለች።