ሙሉዓለም መስፍን ወደ ሠራተኞቹ ቤት አምርቷል

የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሙሉአለም መስፍን የወልቂጤ ከተማ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል።

በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እየተመራ በሀዋሳ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን መስራት የጀመሩት ወልቂጤ ከተማዎች ክፍተት ባላቸው ቦታ ላይ ተጫዋቾችን እያስፈረሙ የሚገኝ ሲሆን የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነውን ሙሉአለም መስፍንን የክለቡ 12ኛው ፈራሚ አድርጎታል።

የእግር ኳስ ህይወቱን በአርባምንጭ ከተማ ጀምሮ በመቀጠል በሲዳማ ቡና ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም በድጋሚ ወደ ሲዳማ ተመልስ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሲጫወት የነበረው አማካዩ በእግር ኳስ ህይወቱ አራተኛ ክለቡ ወደሆነው ወልቂጤ ከተማ ማምራቱ ዕርግጥ ሆኗል።