ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲስ ክለብ ተቀላቀሉ

በቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ተጫውቶ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ።

ከሳምንታት በፊት ሞልደ ባደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ተሳታፊ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሀሩን ኢብራሂም ለተጨማሪ ልምድ Sirius ለተባለ በስዊድን Allsvenskan ሊግ ተሳታፊ ለሆነ ክለብ በአንድ ዓመት የውሰት ውል ተቀላቀለ።

ከዚህ በፊት GAIS እና Angered BK በተባሉ ሁለት የስዊድን ክለቦች ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች በዛሬው ዕለት ከክለቡ ጋር ልምምድ የጀመረ ሲሆን ቀጣይ ቅዳሜ ከ ሀልምስታድ በሚያደርገው ጨዋታ በቋሚነት ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለተኛው በአዲስ ክለብ የውድድር ዓመቱን የጀመረው በመስመር እና በፊት አጥቅነት መጫወት የሚችለው ታሪኩ ደ ቪሳር ነው። በኔዘርላንድ ዝቅተኛው ዲቪዝዮን በሚሳተፈው PEC Zwolle ከአስራ ሰባት ዓመት በታች ቡድን ውስጥ በመጫወት ላይ የቆየው ይህ የአስራ ሰባት ዓመቱ ታዳጊ አሳዳጊ ክለቡን በመልቀቅ በዋናው ቡድን የመጫወት ዕድል ለሚሰጠው VV Nunspeet Jugend ለተባለ ክለብ ፊርማውን በማኖር የውድድር ዓመቱን ጀምሯል።

ከፊርማው በኋላ ከክለቡ ድህረገፅ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ክለቡን መቀላቀሉ ደስታ እንደፈጠረለት በመግለፅ ከክለቡ ጋር ውጤታማ ለመሆን እንደሚሰራ ተናግሯል።