ኃይቆቹ ዩጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ አስፈርመዋል

ሀዋሳ ከተማ የቀድሞውን የፈረሰኞቹ ተጫዋች በስብስቡ ማካተት ችሏል።

የነባር ተጫዋቾች ውል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ወደ ዝግጅት የገቡት ሀዋሳ ከተማዎች ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያሳለፈው ዩጋንዳዊው ቻርለስ ሉክዋጎን የግላቸውን አድርገዋል።

የእግርኳስ ህይወቱን ፕሮላይን በተባለ የሀገሩ ክለብ ጀምሮ ለቪክቶርያ ዩኒቨርስቲ ፣ ልዌዛ እና KCCA መጫወት የቻለው ግብ ጠባቂው ከቅዱስ ግዮርጊስ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁ ተከትሎ ስሙ ከአንዳንድ የሀገሩ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ቢቆይም መዳረሻውን ሀዋሳ ከተማ አድርጓል።

ከረጅም ጊዜ በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ ምርጫ የተዘለለው ሉኩዋጎ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ለሀዋሳ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።