ኢትዮጵያ መድን የውጪ ዜጋ አስፈርሟል

ኢትዮጵያ መድን ናይጀሪያዊውን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የግሉ አድርጓል።

በለቀቁባቸው ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈርም እና የነባሮቹን ውል በማደስ የተጠመዱት ኢትዮጵያ መድኖች የአንድ ናይጀርያዊ አጥቂ ዝውውር አጠናቀዋል። መድኖች ከቀናት በፊት የተከላካዩን ማታይ ሉል ዝውውር ካጠናቀቁ በኋላ ዛሬ ኦቢና ኤቢኔዘር የተባለውን ናይጀርያዊው አጥቂ ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

ከዚህ በፊት በሀገሩ ናይጀርያ ሁለተኛ የሊግ እርከን ለሚሳተፈው ባሪጋ ፕሮፌሽናል ለተባለ ክለብ ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ ተጫዋች በርካታ የማጥቃት ባህሪ ያላቸውን ተጫዋቾች ያጣው የኢትዮጵያ መድን የማጥቃት ክፍል ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።