ፈረሰኞቹ የመስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተስማሙ

ለካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ዛሬ ወደ ግብፅ የሚያቀኑት ፈረሰኞቹ የመስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል።

የ2016 የዝውውር መስኮት ሊዘጋ ቀናቶች በቀሩበት በአሁኑ ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ የመስመር ተከላካዩን አማኑኤል እንዳለን ለማስፈረም መቃረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣላች።

የእግርኳስ ህይወቱን በሲዳማ ቡና የጀመረው አማኑኤል ያለፉትን ሰባት ዓመታት በሲዳማ ቤት መቆየት የቻለ ሲሆን ሁለተኛ ክለቡ በመሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ለሁለት ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል። ተጫዋቹ በአሁን ወቅት ከቡድኑ ጋር አብሮ ልምምድ እየሰራ መሆኑንም ለመታዘብ ችለናል።