ሁለቱ የሴቶች ሊጎች የሚጀምሩባቸው ቀናት ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የሚጀምሩባቸው ቀናት ይፋ ተደርገዋል።

የአዲሱን ዓመት መግባት ተከትሎ የሀገራችን የእግርኳስ ሊጎች ወደ ውድድር በመመለስ ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትናንት ሁለት የመክፈቻ ጨዋታዎችን ያስተናገደ ሲሆን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ደግሞ በወረሀ ጥቅምት አጋማሽ እንደሚጀምር ይጠበቃል። በሴቶች እግርኳስ በኩል የሁለቱ ሊጎች ጅማሮ መቼ እንደሚሆን ደግሞ ከደቂቃዎች በፊት ታውቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በማህበራዊ ገፆቹ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ህዳር 2 እንዲሁም የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ደግሞ ህዳር 22 እንደሚጀመሩ ተገልጿል። ፌደሬሽኑ ጨምሮ እንዳስታወቀው በሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ዝውውር እና ምዝገባ እስከ መስከረም 25 እንዲያገባድዱ ሲገልፅ በሴቶች ከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች ደግሞ እስከ ጥቅምት 20 ድረስ ዝውውር እንዲያከናውኑ አሳስቧል።