የአሰልጣኞች አሰልጣኝ | ሀምበሪቾ ዱራሜ 1-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ

“ያገኘነውን ያለ መጠቀም ችግር ዛሬም አይተናል” አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ

“ብዙ ኳሶችን ስተናል ፣ ነገር ግን ተመጣጣኝ እና ጥሩ ጨዋታ ነበር” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉ ሁለተኛ ድሉን ሀምበሪቾ ላይ ካስመዘገበ በኋላ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ – ሀምበሪቾ ዱራሜ

ስለ ጨዋታው …

“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፣ የጀመርንበት አጀማመር ምናልባት አሁንም ያገኘነውን ያለ መጠቀም ችግር ዛሬም አይተናል። ትንሽ ሁለተኛው ጎል ሲገባብን አሁንም የባለፈው ዓይነት ስህተት እንደ ቡድን ሰርተናል ፣ እርሱን ለማረም እንሰራለን።”

ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር በሁለተኛው አጋማሽ ስለመቀዛቀዛቸው…

“ባለፈው ከተፈጠረው ነገር አኳያ ተጠንቅቀን ለመጫወት የተወሰኑ ደቂቃዎችን ተነጋግረን ነበር የገባነው። እንደባለፈው ነቅለን እንሄድና ኳሱን ይዘነው በቡድን የመጨረሻው ሜዳ ላይ ለመግባት
ነው። በዛ መሐል ነው ምናልባት ያን ለማድረግ ነው ድካም ነው ብዬ ሙሉ በሙሉ ባልልም ያቺን ስቴፕ ለመጠቀም ነበር። ጊዮርጊስ ብዙ ጊዜ በሁለተኛው ፈጥኖ ስለሚያጠቃ ያንን ለመቆጣጠር ወደ ኋላ አፈግፍገን ነበር።”

ከልምድ አንፃር ስለሚታዩ መቆራረጦች…

“መጥፎ አይደሉም ጥሩ ቴክኒክ ያላቸው ኳሱን የሚችሉ ልጆች ናቸው። ምናልባት የጨዋታ ልምድ ይቀራቸዋል ፣ የወዳጅነትም ብዙም ሳናደርግ ነው የመጣነው ከጨዋታ ጨዋታ ያስተካክሉታል። ጥሩ ናቸው ፤ ፕሪምየር ሊግ እንደ መጀመሪያው እንደመሆኑ ያደረጉት ነገር በሒደት የተሻለ ነገር ስህተቶቻችን እየቀነስን እንመጣለን ግን እንደተባለው ልምድ ወሳኝ ነው። እርሱን ደግሞ የምታገኘው ከጨዋታ ስለሆነ ያንን እየተጫወትን ነጥብ መጣሉ ክፋት ቢኖረውም ለማስተካከል እንሄዳለን”።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለ ጨዋታው…

“ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር ፣ እኛም ሆነ ተቃራኒያችን በጣም ጥሩ ነበር የተጫወትነው በጣም ጥሩ ጨዋታን የሚጫወት ቡድን ነው። ሀምበሪቾ ጥሩ ቡድን ነው ማድረግ ይችላሉ ጥሩ ነገር እየሰሩ ነበር። እኛም ከዚህም በላይ ማድረግ እንችላለን ብዙ ኳሶችን ስተናል ነገር ግን ተመጣጣኝ እና ጥሩ ጨዋታ ነበር ጨዋታውን አሸንፈን ወጥተናል።”

ተከታታይ ድሉ ስለሚፈጥረው መልካም ገፅታ…

“ተከታታይ ድልነቱ ሳይሆን ከፊታችን ከፊታችን ያለውን ጨዋታ በጥሩ ነገር ከስህተቶቻችን ተምረን የተሻለ ነገር ለማድረግ ነው ሁሌም የምንሄደው እንጂ ጨዋታን መሸነፋችን ማሸነፋችን ሳይሆን የተሻለ ነገርን ለማድረግ ከዚህ ጨዋታ ለሚቀጥለው ጨዋታ ጥሩ ግብዓት ይሆነናል እና እርሱ ላይ ሰርተንበት የተሻለውን ጨዋታ ለመጫወት ነው የምንፈልገው።”

ስለ ፋሲል ገብረሚካኤል የፍፁም ቅጣት ምት ማዳን …

“ጥሩ ተጫዋች ነው ፋሲል እንደሚያድን ስለማውቅ ነበር አቤልን ጠርቼ ‘ይሄንን በይው’ አልኩት ፤ የሚመለሰውን ኳስ እነርሱ እንዲከላከሉ ግን በትክክል አድኖታል። ጨዋታው ሊቀየር ይችላል ግን ያለን አማራጭ መጠቀም ችለን የተሻለ ውጤት ይዘን ወጥተናል ብዙ ኳሶች አምክነናል ፣ ብዙ ኳሶችን ሞክረናል። ቶሎ ቶሎ ኳሶችን እናደርሳለን ያ ትልቅነታችንን እና ጥሩ ተጫዋቾች እንዳሉኝ ነው የሚያሳየኝ ከዚህም በላይ የተሻለ ነገር እንዲያደርጉ ስራ ይጠብቀኛል።”