ሉሲዎቹ ጥሪ ተደርጎላቸዋል

በ2024 ኦሊምፒክ የሴቶች እግርኳስ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።

ፓሪስ ላይ በሚደረገው የ2024 ኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ቻድን በድምር ውጤት 10-0 በማሸነፍ ወደ ደጣዩ ዙር ያለፉት ሉሲዎቹ በቀጣይ ቀናት ናይጄሪያን በደርሶ መልስ ይገጥማሉ። ጥቅምት 14 አዲስ አበባ ላይ እንዲሁም ጥቅምት 20 አቡጃ ላይ ለሚደረጉት ለእነዚህ ጨዋታዎች የተጠሩትን ተጫዋቾች ዝርዝር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ገፆቹ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ነገ ከ08:00 ጀምሮ ጁፒተር ሆቴል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረበላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር :-

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤተልሔም ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)
አበባ አጄቦ (አዲስ አበባ)

ተከላካዮች

ቤተልሔም በቀለ (መቻል)
ነፃነት ፀጋዬ (መቻል)
ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ)
ብዙአየሁ ታደሠ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ናርዶስ ጌትነት (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ድርሻዬ መንዛ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ሠናይት ሸጎ (አዳማ ከተማ)
ብርቄ አማረ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

አማካዮች

መዓድን ሳህሉ (ሀዋሳ ከተማ)
መሳይ ተመስገን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ንቦኝ የን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አረጋሽ ካልሳ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤተልሔም መንተሎ (አዲስ አበባ ከተማ)
ቤተልሔም ግዛቸው (መቻል)

አጥቂዎች

ሴናፍ ዋቁማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ረድኤት አስረሳኸኝ (ሀዋሳ ከተማ)
ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ)
ሎዛ አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አርያት ኦዶንግ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ንግስት በቀለ (መቻል)
ማህሌት ምትኩ (ሲዳማ ቡና)
እሙሽ ዳንኤል (ሀዋሳ ከተማ)