በዚህ ሳምንት የሚደረጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኙ ይሆን ?

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሦስተኛ ሣምንት ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ላይኖራቸው እንደሚችል እየተገመተ ነው።

ከመስከረም 20 ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በመካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሣምንት መርሐግብሩን በነገው ዕለት ይጀምራል። ሆኖም በሁለተኛው ሣምንት በብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ምክንያት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሳይሰጠው ከቀረ በኋላ የቀጣይ ሣምንት ጨዋታዎችን እንደሚያስተላልፍ ቢታሰብም ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ጨዋታዎቹን ለማስተላለፍ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ እንደማይገኝ አውቀናል። የጉዳዩ ባለቤት ከሆኑት መካከል አወዳዳሪው አካል በዚህ ጉዳይ ላይ ጨዋታዎቹ ሊተላለፉ እንደሚችሉ ቢያውቅም እስካሁን ድረስ ግን እርግጠኛ እንዳልሆኑ ሰምተናል።

*በጉዳዩ ላይ የሚኖሩ አዲስ ውሳኔዎች ካሉ መረጃዎችን እስከ ምሽት ድረስ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።