ሸገር ደርቢ ተራዝሟል

በነገው ዕለት እንደሚደረግ ይጠበቅ የነበረው ጨዋታ እንደማይከናወን ተረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ሲቀጥል ከመርሐ ግብሮቹ መካከል የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ የሚጠበቅ ነበር። ሆኖም ሊግ ካምፓኒው ከደቂቃዎች በፊት ባጋራው መረጃ መሰረት የነገው ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ታውቋል። ጨዋታው ስለተራዘመበት ምክንያት ግን ሊግ ካምፓኒው ያለው ነገር የለም።