ሸገር ደርቢን መቼ ለማድረግ ታስበ ?

በሰባተኛ ሳምንት መካሄድ የነበረበት የሸገር ደርቢ በመያዝነው ወር መጨረሻ ለማድረግ መታሰቡን አውቀናል።

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሜዳ መካሄድ ከጀመረ ስምንተኛ ሳምንት ላይ ደርሷል። በ7ኛ ሳምንት መካሄድ ከነበረባቸው ጨዋታዎች መካከል የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ አክስዮን ማኀበሩ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ማሳወቁ ይታወቃል። በወቅቱ ጨዋታው ስለተራዘመበት ምክንያት ሊግ ካምፓኒው ያለው ነገር ባይኖርም በቀጣይ ይህን ተጠባቂ ጨዋታ ለማካሄድ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ሰምተነናል።

ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘቸው መረጃ ከሆነ ደርቢውን እሁድ ታኀሳስ 21 ቀን በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ለማካሄድ ታስቧል። ይህንን ተከትሎም አወዳዳሪው አካል ከሚመለከታቻው አካላት ጋር በመነጋገር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ሰምተናል። እንቅስቃሴው ተሳክቶ ቦታው እና ቀኑ ከፀና አልያም ለውጥ ከተደረገበት ተከታትለን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል።