የዘንድሮው ኢትዮጵያዊያን የፊፋ ዳኞች ታውቀዋል

በ2024 የፊፋ የዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ኃላፊነት የሚሰጣቸው ኢትዮጵያዊያን የጨዋታ አመራሮች ታውቀዋል።

ዓለምአቀፉ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ ዛሬ ባሳወቀው መሠረት ከኢትዮጵያ ከተላኩለት ዕጩ ዳኞች መካከል ከአንድ ረዳት ዳኛ ውጪ ያሉ አመራሮችን ተቀብሏል።

በዚህም መሠረት በወንዶች ዋና ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ እና  ረዳት ዳኛ አሸብር ታፈሰ በሴቶቹ ደግሞ ዋና ዳኛ ማርታ መለሰ በዝርዝሩ አዲስ የተካተቱ ዳኞች መሆናቸው ታውቋል። በተያያዘ ዜናም ከተላኩ ዕጩ ረዳት ዳኞች መካከል የነበረው ሲራጅ ኑርበገን ከዝርዝሩ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል።

ፊፋ ያጸፀቃቸው ኢትዮጵያውያን የ2024 ኢንተርናሽናል የጨዋታ አመራሮች ዝርዝር ከታች በምስሉ ላይ ይገኛል።