ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ | መሪው ነጌሌ አርሲ ነጥብ ጥሏል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ዛሬ ጅማሮውን ሲያደርግ በምድብ ለ በዛሬው ዕለት ሶስት ጨዋታዎች ተደርገው ሁለቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። ደብረብርሃን ከተማ ደግሞ ብቸኛ የምድቡ ባለድል ሆኗል።

የመጀመሪያ አጋማሽ ቀዝቀዝ ብሎ በጀመረው በአራቱ ሰዓቱ ጨዋታ ጋሞ ጨንቻ ከደብረብርሃን ከተማ ተገናኝቶ በደብረብርሃን 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። በአንደኛው ምንም አይነት የግብ ሙከራዎችን ያላስመለከተው በዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ሳያደርጉ 0ለ0 በሆነ ውጤት ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ ሁለቱም ቡድን ተሻሽሎ መግባት ችለዋል።በተለይም ደብረብርሃን ከተማ ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር የተሻለ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በ80ኛው ደቂቃ ተቀይሮ የገባው በሀይሉ ተሻገር በእርስ በርስ ቅብብሎሽ በመሄድ ኳስና መረብ አገናኝቶ ደብረብርሃን ከተማን መሪ አድርጓል።

ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ የአቻነት ግብ በመፈለግ ጫና ፈጥሮ በመጫወት ኳስ ወደፊት ገፍተው ሲጫወቱ የተስተዋለው ጋሞ ጨንቻ በ89ኛው ደቂቃ የፊት መስመር ተጫዋቻቸው ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በመረብ አጋኝቶ አቻ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

ባለቀ ደቂቃ ብዙ የግብ ሙከራዎችን ያስመለከተን ይሄ ጨዋታ ተጨማሪ በታየው በ95ኛው ደቂቃ ያገኙትን የመጨረሻ እድል የሆነው ማዕዘን ምት አብዱልመጅድ ሀሰን ቀጥታ ወደግብ መጥቶ ኳስና መረብ አገናኝቶ ጨዋታው 2ለ1በሆነ ውጤት በደብረብርሃን ከደማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ከሰዓት 8፡00 ላይ ኦሜድላ እና ቦዲቲ ከተማን ያገናኘው መርሃ ግብር ያለግብ 0ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ብዙ የግብ ሙከራዎችን እና ማራኪ የኳስ እንቅስቃሴ በተመለከትንበት በዚህ ጨዋታ ቦዲቲ ከተማ በመጀመሪያ አጋማሽ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አገንቶ ሳይጠቀሙ ቀርቷል። ኦሜድላ በአንፃሩ ረጃጅም ኳሶችን በመጫወት የግብ ሙከራዎቸን ያደረገ ሲሆን በተቃራኒ ቡድን ጀርባ ረጃጅም ኳሶችን በመጣል ጥሩ ጥሩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ተመልከተናል።

ሁለቱም ቡድን ነጥብ ፍለጋ ብዙ ሙከራዎችን ሲያደረጉ ቢንመለከትም ቦዲቲ ከተማ የተሻለ የኳስ ቀለጥጥር አድርጓለሰ።ሆኖም ግን ጠንከር እና ረጃጅም የተከላካይ መስመር ተጫዋቾችን የያዘውን ኦሜድላ ከተማን አልፎ ግብ ማስቆጠር ተስኗቸው ሁለቱም ቡድን ነጥብ ተጋርቷል።

የምድብ ለ የመጀመሪያ ቀን የመጨረሻ ጨዋታ የነበረው የምድብ መሪ የሆነውን ነጌሌ አርሲን ከየካ ክፍለ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። በመጀመረያ አጋማሽ የምድብ መሪነቱ ለማጠናከር ጠንከር ብሎ የገባው ነጌሌ አርሲ ገና ጨዋታውን እንደጀመረ ጫና ፈጥሮ በመጫወት የኳስ ብልጫ ወስዷል።ሆኖም ግን የምድብ ደረጃውን ለማሻሻል ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተሰተዋለው የካ ክፍለከተማ ጥሩ ፉክክር አድርጓል።

ነጌሌ አርሲ ቀዳሚ ለመሆን ግብ ፍለጋ ሁሉም ወደፊት በሚሄዱበት ቅፅበት የየካ ክፍለከተማ ተከላካዮች ኳስን በማስጣል በመልሶ ማጥቃት በእርሰስ በርስ ቅብብሎሽ በ23ኛው ደቂቃ በብስራት ታምሩ ግብ መሪ ሆነዋል። ወሳኝ ነጥቡን ለመውሰድ የአቻነት ግብ ፍለጋ በተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የተሰተዋሉት ነጌሌዎች የመጀመሪያ አጋማሽ መደበኛው ደቂቃ ሊጠናቀቅ አከባቢ በታምራት ኢያሱ ላይ በተሰራው ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት አግንተው ታምራት እራሱ ኳስና መረብን አገናኝቶ 1ለ1እረፍት ወተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድን የመከላከል ዘዴ ይዞ የገቡ ሲሆን ነጌሌ አርሲ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር አድርጓ የግብ ሙከራዎችን አድርገዋል።የካ ክፍለከተማ በአንፃሩ ከምድብ መሪው ነጥብ ለመጋራት ወደኋላ አፈግፍገው ሲከላከሉ ተስተውለዋል። መደበኛው ደቂቃ ሊጠናቀቅ አከባቢ ነጌሌ አርሲ ጥሩ ጥሩ የኳስ ሙከራዎችነሰ ቢያደርጉም ግብ ማክቆጠር ተስኗቸው በመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠሩ ግቦች 1ለ1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

የምድብ ለ ጨዋታዎች ነገም ቀጥለው ሲደረጉ 3:00 ሸገር ከተማ ከደሴ ከተማ፣5:00 ወሎ ኮምቦልቻ ከባቱ ከተማ፣8:00 ካፋ ቡና ከቢሾፍቱ ከተማ፣10:00 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።