የቀጣይ ሣምንታት ጨዋታዎች የቀን ሽግሽግ ተደርጎባቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የቀጣይ ሦስት ሣምንታት ጨዋታዎች ላይ የቀን ሽግሽግ ማድረጉን የሊግ አክሲዮን ማኅበሩ ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ 9ኛ እስከ 11ኛ ሣምንት ያሉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖራቸው ባስነበብንበት የትናንት ዘገባችን ላይ የእነዚህ ሣምንታት መርሐግብር የቀን ሽግሽግ ሊደረግበት እንደሚችል በጠቀስነው መሠረት የሊግ አክሲዮን ማኅበሩ ቀጣዩ (9ኛው ሣምንት) ሐሙስ ታኅሣሥ 25 እንደሚደረግ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም ወደ ረቡዕ ታኅሣሥ 24 ቀደም ብሎ እንዲደረግ ሲወስን በየሣምንታቱ የነበሩ የሦስት ቀናት ልዩነቶችን ወደ ሁለት ዝቅ እንዲሉ ተወስኗል።