የተቋረጠው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ታውቋል


5ኛ ሣምንቱ ላይ ደርሶ ለሴቶች  ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበትን ቀን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ምክንያት 5ኛው ሳምንት ላይ መቋረጡ ይታወቃል። ሆኖም ውድድሩ የካቲት 9 ላይ ከተቋረጠበት እንደሚቀጥል የውድድር ዳይሬክቶሬት ማሳወቁን ፌዴሬሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ይፋ አድርጓል።