አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆናለች

አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆና ተሹማለች።

በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያ በመጪው የካቲት ደቡብ አፍሪካን የምትገጥም ሲሆን ለዚህ የማጣርያ ውድድር አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆና መሾሟን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።


የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ተጫዋች ራውዳ በክለብ ደረጃ ለየካ ሚካኤል ፣ ክዊንስ ኮሌጅ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ለምርት ገበያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሴት ቡድኖች ተጫውታ ያሳለፈች ሲሆን ወደ አሰልጣኝነት ተሸጋግራ በተለያዩ አካዳሚዎች ከሠራች በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆናም ሠርታለች። በአሁኑ ሰዓትም በቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝነት በመስራት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል።