የአፍሪካ ዋንጫ | የማሊ እና ኮትዲቯር ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያዊ ባለሙያ ተመድበዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ተጠባቂ የምሽት ጨዋታ ላይ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ሙያዊ ግልጋሎት እንዲሰጡ ተመድበዋል።

34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኮትዲቫር አዘጋጅነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። በዚህ ውድድር ላይም ሦስት ኢትዮጵያዊ ባለሙያዎች ሙያዊ ግልጋሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ወደ ፍፃሜው እየተቃረበ የሚገኘው ውድድሩ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት መከወን የጀመረ ሲሆን ዛሬም በተጠባቂ ፍልሚያዎች ይቀጥላል። በዚህም ምሽት 2 ሰዓት ላይ ማሊ ከአዘጋጇ ሀገር ኮትዲቯር ጋር የምታደርገው ጨዋታ ይከናወናል።

ይህንን ጨዋታም የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከኬኒያዊ ባልደረባቸው ሚኬል አሜንጋ ጋር በጣምራ በመሆን የቴልኒክ ጥናት እንዲያከናውኑ ምደባ እንደተደረገ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።