ለድሬ ዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ አድርጓል

ከየካቲት 16 ጀምሮ በሦስት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ለሚደረገው የድሬ ዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፉ ታውቋል።

የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የሰው ሰራሽ ሣር ተከላ ማጠናቀቁን ተከትሎ በደመቀ ስነስርዓት መክፈቻውን ለማካሄድ በመታቀዱ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በጎፈሬ የስፖርት ትጥቅ ብራንድ አማካኝነት በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙ ሦስት ሀገራት መካከል ውድድር የሚደረግ በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት 30 ተጫዋቾች ነገ የካቲት 13 ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉ ታውቋል።


ግብ ጠባቂዎች

ፍሬው ጌታሁን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አብዩ ካሳየ – ድሬዳዋ ከተማ
አላዛር ማርቆስ – ባህር ዳር ከተማ

ተከላካዮች

እንዳለ ዮሐንስ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፍቅሩ ዓለማየሁ – አዳማ ከተማ
ጊት ጋትኮች – ሲዳማ ቡና
የአብሥራ ሙሉጌታ – ሻሸመኔ ከተማ
ብርሃኑ በቀለ – ሲዳማ ቡና
ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ግሩም ሀጎስ – መቻል
ያሬድ ካሳየ – ኢትዮጵያ መድን
ዳዊት ማሞ – መቻል

አማካዮች

አለልኝ አዘነ – ባህር ዳር ከተማ
አብነት ደምሴ – ወላይታ ድቻ
ብዙዓየሁ ሰይፉ – ወላይታ ድቻ
አፍቅሮተ ሰለሞን – ሀምበርቾ
በረከት ግዛው – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብሩክ ማርቆስ – ሀዲያ ሆሳዕና
እንዳልካቸው መስፍን – አርባምንጭ ከተማ
አናንያ ጌታቸው – ጅማ

አጥቂዎች

ኪቲካ ጅማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቢኒያም ዐይተን – አዳማ ከተማ
ዮሴፍ ታረቀኝ – አዳማ ከተማ
በረከት ወንድሙ – ሀምበርቾ
ኢዮብ ዓለማየሁ – ሀዋሳ ከተማ
ቦና ዓሊ – አዳማ ከተማ
ቢኒያም ፍቅሩ – ወላይታ ድቻ
ቢኒያም ጌታቸው – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፋሲል አስማማው – ሸገር ከተማ
ታምራት ኢያሱ – ቅዱስ ጊዮርጊስ