የጣና ሞገዶቹ የመስመር አጥቂ አስፈርመዋል

ዘንድሮው የውድድር ዓመት እንደ ዕቅዳቸው ያልሄደላቸው ባህር ዳር ከተማዎች የመስመር አጥቂ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ በመጀመሪያ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድራቸው ጠንካራ ሆነው የታዩት ባህር ዳር ከተማዎች የ2016 የውድድር ዘመን እንደጠበቁት እየሄደላቸው አይገኝም።

ቡድኑ ዱሬሳ ሹቢሳ እና አደም አባስን ባጣበት የመስመር አጥቂ ቦታ ላይ የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች የሆነውን ጸጋዬ አበራን ወደ ስብስቡ መቀላቀሉ ታውቋል።