ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጓል

በጋና ዋና ከተማ አክራ በሚዘጋጀው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ18 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል።


ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 15 በጋና ዋና ከተማ አክራ የሚዘጋጀው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በወንዶቹ ዘጠኝ በሴቶቹ ደግሞ ስምንት ሀገራትን በሁለት ምድብ ከፍሎ በውድድሩ የሚያሳትፍ ሲሆን በሴቶች ዘርፍ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም ተሳትፎ የሚኖረው ይሆናል። ሆኖም በቅርቡ ለብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ 18 ተጫዋቾች ከነገ ጀምሮ በቱሊፕ ሆቴል እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።

ግብ ጠባቂዎች

አበባ አጂቦ – አዲስ አበባ ከተማ
ገነት ኤርሚያስ – አርባምንጭ ከተማ
መስከረም መንግሥቱ – ሀዋሳ ከተማ

ተከላካዮች

ድርሻዬ መንዛ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብርቄ አማረ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ናርዶስ ጌትነት – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብዙዓየሁ ታደሰ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ትዕግሥት አዳነ – ሀዋሳ ከተማ
ባንቺይርጋ ተስፋዬ – አርባምንጭ ከተማ

አማካዮች

አረጋሽ ካልሳ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ንቦኝ የን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
እፀገነት ግርማ – ሀዋሳ ከተማ
ማዕድን ሳህሉ – ሀዋሳ ከተማ
ትውፊት ካዲዮ – አርባምንጭ ከተማ

አጥቂዎች

እሙሽ ዳንኤል – ሀዋሳ ከተማ
ቱሪስት ለማ – ሀዋሳ ከተማ
ረድዔት አስረሳኸኝ – ሀዋሳ ከተማ
መሳይ ተመስገን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች መርሐግብር 👇

የካቲት 30/2016 ከጋና
መጋቢት 3/2016 ከዩጋንዳ
መጋቢት 6/2016 ከታንዛኒያ