ሀዋሳ ከተማ የቀድሞው ተጫዋቹን አስፈርሟል

አጥቂው እስራኤል እሸቱ የልጅነት ክለቡን በይፋ ተቀላቅሏል

የሁለተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታን በነገው ዕለት ፋሲል ከነማን በማስተናገድ የሚጀምሩት ሀዋሳ ከተማዎች ሙጂብ ቃሲምን ባጡበት እና ቡድኑንም በማጥቃቱ ረገድ ያለበትን ክፍተት ለመሸፈን ይረዳው ዘንድ በዛሬው ዕለት እስራኤል እሸቱን እስከ ዓመቱ መጨረሻ በይፋ ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በሀዋሳ ከተማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ውስጥ በመጫወት እግር ኳስን የጀመረው እና በዋናውም ክለብ ዘለግ ያሉ ዓመታትን በማሳለፍ በመቀጠል ደግሞ በሰበታ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ እና መቻል ቆይታን ያደረገው የፊት መስመር አጥቂው እስራኤል እሸቱ ያለ ክለብ ጥቂትን ወራትን ካሳለፈ በኋላ አሳዳጊ ክለቡ ሀዋሳን በይፋ ዛሬ ተቀላቅሏል።