ሀዋሳ ከተማ የወጣቱን ግብ ጠባቂ ውል አድሷል

ግብ ጠባቂው ምንተስኖት ጊምቦ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ውሉ በሀዋሳ ተራዝሞለታል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛውን ዙር የውድድር ዘመን በትላንትናው ዕለት ፋሲል ከነማን ገጥሞ ሽንፈት ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ በቀጣዮቹ የሊግ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ የቀድሞው ተጫዋቹ እስራኤል እሸቱን ወደ ስብስቡ የቀላቀለ ሲሆን አሁን ደግሞ የወጣቱን ግብ ጠባቂ ምንተስኖት ጊምቦን ውል እስከ ዓመቱ መጨረሻ አራዝሟል።

በጉዳት ምክንያት ለወራቶች ከሜዳ ርቆ የሰነበተው ግብ ጠባቂው በሀዋሳ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ውስጥ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ያለፉትን ዓመታት በዋና ቡድን ውስጥ እና ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድንም መጫወት የቻለ ሲሆን ከጉዳቱ ማገገሙን ተከትሎ በይፋ ውሉ በክለቡ ተራዝሞለታል።