ሲዳማ ቡና አጥቂ አስፈርሟል

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚመራው ሲዳማ ቡና አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በ16 ጨዋታዎች 18 ነጥቦችን በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሲዳማዎች ክፍተት አለው ባሉበት የአጥቂ መስመራቸው ላይ አንድ ተጫዋች ከአንደኛ ሊግ ማስፈረማቸው ታውቋል።

ክለቡን የተቀላቀለው በዘንደሮው የአንደኛ ሊግ ውድድር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ መለያ 13 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው እና የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ደረጃ እየመራ የሚገኘው ሔኖክ ፍቅሬ ነው። ተጫዋቹ የሙከራ ጊዜ ተሰጥቶት ከቡድኑ ጋር አብሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የውል ዘመኑም ለአንድ አመት መሆኑ ታውቋል።

ፎቶ : ዳጉ ስፖርት