ሲዳማ ቡና ጋናዊውን አማካይ አስፈርሟል

ባለፉት ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ ፣በመቻል እና በአርባምንጭ ከተማ የምናውቀው ተጫዋች ሲዳማን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።

በአሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚመሩት ሲዳማ ቡናዎች ከትናንት በስትያ ሔኖክ ፍቅሬን ከአንደኛ ሊግ ማስፈረማቸው ይታወሳል።00 አሁን ደግሞ ክለቡ ጋናዊውን የተከላካይ አማካይ ኢማኑኤል ላሪያን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረሙን ገልፆል።

ከዚህ ቀደም 2010 ላይ ወደ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል በማምራት ለድሬዳዋ ከተማ ለአንድ ዓመት ተጫውቶ የነበረው ኢማኑኤል ላሪያ ከብርቱካናማዎቹ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ጃፓን ካመራ በኋላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በመቻል እና በአርባምንጭ ቆይታ ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ በድሬደዋ አብረውት ከሰሩት ከአሰልጣኝ ዘላለም ጋር ዳግም አብሮ ለመስራት ፊርማውን ማኖሩ ተረጋግጧል።