ቅዱስ ጊዮርጊስ አማካይ አስፈረመ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሲጫወት የቆየው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ መቀላቀሉን ይፋ አድርጓል።

ክንድዓለም ፍቃዱ ፈረሰኞቹን የተቀላቀለው ተጫዋች ነው። ባቱ ከተማን በመልቀቅ የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሸገር ከተማን በዘንድሮው የውድድር ዓመት ተቀላቅሎ እስከ ውድድር ዘመኑ አጋማሽ ድረስ ያሳለፈው የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ፣ ሰበታ ከተማ፣ ሀላባ ከተማ እና ሻሸመኔ ከተማ አማካይ ለቀጣዩ አንድ ዓመት በቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያቆየውን ውል ማሰሩን ክለቡ አሳውቋል።

ፈረሰኞቹ በዝውውር መስኮቱ አጥቂው ታምራት ኢያሱን አስፈርመው የአብስራ ተስፋዬን ወደ ዋና ቡድን ማሳደጋቸው ይታወቃል።