መቻል ከተከላካይ አማካዩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

ያለፉትን አንድ ዓመት ከስድስት ወር በመቻል ቆይታ የነበረው የተከላካይ አማካዩ ከቡድኑ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል።


ከዓመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እየተፎካከረ የሚገኘው መቻል ከቡድኑ ስብስብ ውስጥ ከአንድ ተጫዋች ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል። ተጫዋቹም ተስፋዬ አለባቸው ሲሆን ያለፉትን አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከቡድኑ ጋር ቆይታ በማድረግ ግልጋሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። ከሰሞኑን ምክንያቱ በግልፅ ባይታወቅም ከቡድኑ ጋር አብሮ ልምምድ መስራት ያቆመ ሲሆን ተስፋዬ ከቀሪ የስድስት ወር ውል እያለው ዛሬ ከቡድኑ ጋር በስምምነት መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

ተስፋዬ ከዚህ ቀደም በሰበታ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በወልድያ እና በሀድያ ሆሳዕና ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል።