የነገውን የወዳጅነት ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታውቀዋል

ዋልያዎቹ ከአዞዎቹ ጋር የሚያደርጉትን የወዳጅነት ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ሲታወቁ ጨዋታውም ያለ ተመልካች እንደሚደረግ ተረጋግጧል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ 9 ሰዓት ላይ በአንጋፋው አዲስ አበባ ስታዲየም ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርገውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ የሚመሩት ሦስት የጂቡቲ እና አንድ የኢትዮጵያ ዳኞች ታውቀዋል።

በዚህም መሠረት መሐመድ ዲራኔህ ጉዒዲ በዋና ዳኝነት ፣ ኤሌየህ ሮብሌህ ዲሪር እና ራቺድ ዋይስ ቦውራሌህ በረዳትነት እንዲሁም ኢትዮጵያው ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት ይመሩታል።


በተያያዘ ዜና የነገው ጨዋታ የስታዲየሙ ዕድሳት ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ምክንያት ያለ ተመልካች እንደሚደረግም ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።