ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ | ሀላባ ከተማ የእለቱ ብቸኛ ባለድል ሆኗል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ”ሀ” 17ኛው ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሦስት ጨዋታዎች ሲገባደድ ሁለቱ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀው ሀላባ ከተማ የእለቱ ብቸኛ ባለድል ሆኗል።

ረፋድ ሦስት ሰዓት ላይ የተደረገው መርሃግብር ነቀምቴ ከተማ ከኦሮሚያ ፖሊስ ነጥብ ተጋርተዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ ኦሮሚያ ፍፁም የጨዋታ በላይነት በወሰደበት በዚህ ጨዋታ ግቦች መቆጠር የጀመሩት ገና በስድስተኛው ደቂቃ ነበር። ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ ለግብ ከተቃረቡ ሙከራዎች ጋር ያደረጉት ኦሮሚያ ፖሊሶች የመጀመሪያ ግብ ለማስቆጠር ስድስት ደቂቃ ብቻ ነበር የጠበቁት። በ6ኛው ደቂቃ ቢቂላ ሲሪቃ ኳስን እየገፋ በመሄድ ከግብ ክልል ውጪ ሆኖ የመታት ኳስ ከመረብ ጋር ተገናኝታ ኦሮሚያ ፖሊስን መሪ እንዲሆን አስችላለች።

በመልሶ ማጥቃት የግብ እድል ለመፍጠር ሲጣጣሩ የነበሩት ነቀምቴዎች በ8ኛው ደቂቃ የኦሮሚያ ፖሊሱ ግብ ጠባቂ በነቀምቴ ከተማው ሰለሞን ጌታቸው ላይ በሰራው ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት ነቀምቴ ከተማ ቢያገኙማ ሰለሞን ጌታቸው እራሱ ቢመታም ግብ ጠባቂው ዶት ዳንኤል መልሶበታል። ፍፁም ከተማ በማምከን መረጋጋት የተሳናቸው ነቀምቴዎች በሰሩት ስህተት የተገኘውን ኳስ በ11ኛው ደቂቃ ዳንኤል ዳርጌ ከግብ ክልል ውጪ ሆኖ በመምታት ሁለተኛ ግብ ለኦሮሚያ ፖሊስ አክሏል። በ17ኛው ደቂቃ ታረቀኝ ታደሰ በመስመር በኩል ኳስ ይዞ በመግባት የመታትን ኳስ ግብ ጠባቂው ሲመልስበት ኳሷን ሲጠባብቅ የነበረው ተመስገን ዱባ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር ነቀምቴ ከተማን ወደጨዋታ መልሷቸዋል።ከግቧ በኋላ ነቀምቴ ከተማ በመነቃቃት ሲጫዎትም የተሰተዋለ ሲሆን የመጀመሪያ አጋማሽ 2ለ1 እየተመሩ ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ከእረፍት መልስ ኦሮሚያ ፖሊስ የተቀዛቀዘ የጨዋታ እንቅስቃሴ ያደረገበትን ሁለተኛ አጋማሽ ለማሳለፍ ሲገደዱ የቀምቴዎች በአንፃራቸው የጨዋታ እንቅስቃሴ ብልጫ መውሰድ ችለዋል። በዚህም በተደጋጋሚ የኦሮሚያ ፖሊስ ግብ ለመድፈር የግብ ማግባት ሙከራ ሲያደርጉ ለመመልከት ተችሏል። ከበርካታ የግብ ሙከራ በኋላም የጥረታቸው ውጤት የሆነችዋን የአቻነት ግብ ተቀይሮ በገባው በሬድዋን ናስር አማካኝነት በ77ኛው ደቂቃ በአንድ ለአንድ ቅብብል ሰለሞን ጌታቸው ኳሱን ጨርሶ አቃብሎት በግሩም ሁኔታ መረብ ላይ አሳርፎ ሁለት እኩል አድርጓቸው ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ቀን 8:00 ላይ የተደረገው ጨዋታ በይርጋጨፌ ቡና እና በሀላባ ከተማ መካከል ተደርጎ ሀላባ ከተማ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አሳክቷል። ደመቅ ብሎ በመጀመር እየቀዘቀዘ በመጣው በዚህ ጨዋታ በመጀመሪያዎች አስር ደቂቃዎች ሀላባ ከተማ ፍፁም የጨዋተ በላይነት መውሰድ የቻለ ሲሆን አጋጣሚዉን በመጠቀም ግብ በማስቆጠርም ቀዳሚ መሆን ችለዋል። በአስረኛው ደቂቃ ከመስመር የተሻማውን ኳስ ወሰን ጌታቸው በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር ሀላባን ቀዳሚ አድርጓል። ግብ ካስቆጠሩ በኋላም ተጨማሪ ግብ ሀማስቆጠር በመልሶ ማጥቃት ጥረት ቢያደርጉም በይርጋጨፌ ቡናዎች የጨዋታ እንቅሰቃሴ እና ኳስ ቁጥጥር ብልጫ ተወስዶባቸው ተረጋግተው እንኳን ለመጫወት ሲቸገሩ ተሰሰተውለዋል።

ይርጋጨፌ ቡናዎች ምንም እንኳን ቢመሩም የአቻነት ግብ ለማስቆጠር አልፈው አልፈው ቸሚያገኙትን አጋጣሚ ወደግብ ለመቀየር ሲጥሩ ለመመለከት ትቸሏል።ሆኖም ግን ሶስቷን ነጥብ ለማሳካት ወደኋላ አፈግፍገው የተጫወቱትይ ሀላባዎችን አልፈው ግብ ማስቆጠር ተስኗቸው የመጀመሪያ አጋማሽ ተገባዷል።

ጨዋታው ከእረፍት ሲመልስ ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ የተስተዋለ ሲሆን ሀላባ ከተማ ውጤታቸውን ለማስጠበቅ በሙሉ ወደኋላ አፈግፍገው በመከላከል ሰሐጫወቱ ተስተውለዋል።ይርጋጨፌ ቡና በአንፃሩ  ከጀርባ ጀምረው ኳስ   መስርተው በተደጋጋሚ ወደ ተቃራኒ ቡድን በመግባት ግብ ለማግባት ጥረት ቢያደርጉም ጠንካራ ሆኖ የዋለውን የሀላባ ከተማን ተከላካይ መስመር አልፈው ግብ ማስቆጠር ተስኗቸው ጨዋታው ሊገባደድ ተገዷል።በዚህም ጨዋታው 1ለ0 በሀሸነ ጠባብ ውጤት በሀላባ ከተማ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል።

የሳምንቱ ማሳረጊያ ጨዋታ በሁለቱ ጅማ ክለቦች በጅማ አባጅፋር እና በጅማ አባቡና መካከል ተደርጎ ያለግብ ተለያይተዋል። እምብዛም የግብ ሙከራ ባስመለከተው በሳምንቱ እና በእለቱ መጨረሻ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ የማይባል የጨዋታ እንቅስቃሴ ለተመልካች ቢያስመለከቱም ጅማ አባጅፋሮች በመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ማስቆጠር ሚችሉበትን አጋጣሚዎች ሳይጠቀሙ ቀርተዋል። ጅማ አባቡና በአንፃሩ ግብ ለማስቆጠር በረጃጅም ኳስ የሚያደርጉት የግብ ሙከራ ጥሩ ሆኖ የዋለው የጅማ አባጅፋሩ ግብ ጠባቂ ሲመልስባቸው ለመመለከት ተችሏል። ሁለቱም ቡድኖች ሦስት ነጥብ ለማሳካት የገቡ ቢሆንም አስቆጪ የሚባሉ አጋጣሚዎችን አግንተው ሳይጠቀሙ ቀርተው የመጀመሪያ አጋማሽ ያለ ግብ ተለያይተዋል።

ከመልበሻ ክፍል መልስ የመጀመሪያ አጋማሽ የሚመስል የጨዋታ እንቅስሴዎች ተስተውለዋል። ሆኖም ግን ጅማ አባቡና የተጫዋቾች ቅያሪ በማድረግ ጠንከር ብሎ በመግባት የግብ ማግባት ሙከራ ሲያድርጉ ተስተውለዋል። ጅማ አባ ጅፋሮችም በመልሶ ማጥቃት አንዳንድ የግብ ማግባት ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም አጨራረስ ላይ ደካማ ሆኖ ውለዋል። ጥሩ የተንቀሳቀሱት አባቡናዎች እንዲሁ አጋጣሚዎችን ፈጥረው ወደግብነት ለመቀየር ሲቸገሩ ተሰሰውለዋል። በተለይም የጅማ አባ ጅፋሩ ጌታቸው ተፈሪ በሁለት ቢጫ በ85ኛው ደቂቃ ከሜዳ በቀይ ካርድ መሰናበቱ ቀሪዎችን አምስት ደቂቃዎትንና ተጨማሪ ደቂቃዎችን ጫና እንዲፈጥሩ ያደረገ ነበር። ሆኖም ግን ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው ያለግብ ተገባዷል።