የጦሩ የግብ ዘብ ለሀገራዊ ግዴታ ጥሪ ደርሶታል

አልዮንዜ ናፍያን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ይሳተፋል።

በያዝነው የውድድር ዓመት መቻልን ተቀላቅሎ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው ግብ ጠባቂው አልዮንዜ ናፍያን ሀገሩ ዩጋንዳ በምታደርጋቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች እንዲሳተፍ ጥሪ ደርሶታል።


በውድድር ዓመቱ ሀያ አራት ጨዋታዎች ላይ የተሳተፈው ግብ ጠባቂው ሀገሩ ከቦትስዋና እና አልጀርያ ላሉባት ጨዋታዎች በስብስቡ መካተቱን ተከትሎ ለቋሚ ተሰላፊነት ከቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ዋቴንጋ ኢስማ ጋር ይፎካከራል።
ግብ ጠባቂው በ2022 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮና (ቻን) በመሳተፍ ሀገሩን ማገልገል የጀመረ ሲሆን በስድስት ጨዋታዎች ላይም በቋሚነት ጀምሯል።

ተጫዋቹ በሰርቢያዊው አሰልጣኝ ሰርጂዮቪች ሚሎቲን (ሚቾ) ከቀረበለት ጥሪ በፊት ለደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ለመጫወት ከጫፍ ደርሶ እንደነበርም ይታወቃል።